ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ወረታ ግብርና ኮሌጅን “የሳተላይት ግቢ” አደረገ
ከወታደር ማሰልጠኛነት ወጥቶ ለብዙ ዓመታት የግብርና ባለሙያዎች መማሪያ የሆነው የወረታ ግብርና ኮሌጅ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሳተላይት ግቢ (satellite campus) አድርጎ እንዲጠቀምበት ግንቦት 11/2013 ዓ.ም የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሟል፡፡

የአሰራር መመሪያዎች የተካተቱበትን ሰነድ የፈረሙት የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚደንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን እና የወረታ ግብርና ኮሌጅ ዲን አቶ ጥላሁን ባዬ ሲሆኑ የኢፌዴሪ ንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፈንታ ደጀን፣ የአብክመ ም/ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ፈንታ ማንደፍሮ፣ የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ ፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የአገር ሽማግሌዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል፡፡

በወረታ ግብርና ኮሌጅ ሳተላይት ግቢ (satellite campus) በተለያዩ የጥናት መስኮች የተከታታይና ርቀት ትምህርቶችን ለማስጀመር ዩኒቨርሲቲያችን ምዝገባ ላይ ነው፡፡
