Preaload Image

የጎንደር ዩኒቨርስቲ በ2ዐዐ2 ዓም ከመሠረታዊ የስራሂደት ለውጥ (BPR). አተገባበር ጀምሮ በመማር ማስተማር ዓብይ የስራ ሂደት ስር ካቋቋማቸው የማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች ውስጥ በዩኒቨርስቲው ሁሉም ግቢዎች የተቋቋሙት የፈተና ማእከላት ይገኙበታል፡፡ማዕከላቱም በዋናነት ከሲለበስ ዝግጅት ጀምሮ የተከታታይ ምዘናና የማጠቃለያ ፈተና አተገባበርን ወደ ዘመናዊና ጥራቱንና ደረጃውን በጠበቀ አኳኋን እንዲካሄድ ለማስቻል የተቋቋሙ ናቸው፡፡ማዕከላቱ ከዚህም ባሻገር ማንኛውንም የመማር ማስተር ዓላማ ለማሳካት የሚያገለግሉ የማባዛት አገልግሎት በመስጠት የማስተማሪያ ሃንድአውቶች፣ ተከታታይ ፈተናዎች፣ አሳይመንቶች፣ሞጁሎችና የመሳሰሉትን በማባዛት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡በዚህም ካለፉት ጊዜያት በተሻለ መምህራን ሲለበስ በወቅቱና በተገቢው ሁኔታ በማዘጋጀት የተከታተታይ ምዘናን በመተግበርና ፈተናዎች በትምህርት ክፍል ደረጃ በተቋቋሙ የፈተና ኮሚቴዎች ተገምግመው እንዲፀድቁና ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ አበረታች የሚባል ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ ተችሏል፡፡

ከ2ዐዐ7 ዓም ጀምሮ ደግሞ በዩኒቨርስቲው የአደረጃጀት ለውጥ የፈተና ማእከላት በበላይነት በአካዳሚክ ምክትል ኘሬዚዳንቱ ስር በተቋቋመው የፈተና ማዕከላት ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት ስር በሁሉም ኮሌጆች፣ፋኩልቲዎችና ትምህርትቤቶች የተቋቋሙ ሲሆን የየኮሌጆቹ የፈተናማዕከላትም ተጠሪነታቸው ለፈተናማዕከላት ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤትና ለየኮሌጆቹ ዲን ጽ/ቤቶች ይሆናል፡፡

የፈተና ማዕከላት ዳይሬክቶሬት ራዕይ

ዩኒቨርስቲያችን እ.ኤ.አ. በ2ዐ2ዐ ከሌሎች አቻ የሐገር ውስጥና የውጭ ተቋማት ጋር የሚወዳደር የተማሪዎች ምዘና ስርዓት የሚከተል እንዲሆን ማድረግና በዚህም ተመራቂዎቻችን በስራ ዓለም በተጨባጭ ችግርፈቺ እንዲሆ ን ማስቻል

የዳይሬክቶሬቱ መሪ ቃል

 “ደረጃውን በጠበቀና ደህንነቱ በተረጋገጠ የተማሪዎች ምዘና ሰርዓት የትምህርት ጥራትን እናሳካለን”

የፈተና ማዕከላት ዳይሬክቶሬት  ጽ/ቤት ዋና ተግባር

የፈተና ማዕከላት ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት ዋና ተግባር ለሐገራችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ቀጣይነት አስተዋጽኦ የሚያበርክቱ በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት ተወዳዳሪና ችግርፈች ባለሙያዎች እንዲፈጠሩ ደረጃውን  የጠበቀና ሚስጥራዊነቱ የተረጋገጠ ፈተና ማዘጋጀትና ማስፈጸም ነው፡

 በፈተና ማዕከላት ዳይሬክቶሬት ስር በኮሌጅ/ ፋካልቲ/ኢንስቲቲውት/ ት/ት ቤት ስር ያሉ የስራ ሃላፊዎች

ተ.

ስም

ሃላፊነት

 1.  

ወንድወሰን ካሳሁን

የፈተና ማዕከላት ዳይሬክተር

 1.  

ዳንኤል ታደሰ

ግብርና ፋካልቲ ፈተና ማዕከል አስተባባሪ

 1.  

አስቻለው አሰፋ

እንስሳት ህክምና ፋካልቲ ፈተናማ ዕከል አስተባባሪ

 1.  

መሰረት ሃሰን

ስነ-ት/ት ቤት ፈተና ማዕከ ልአስተባባሪ

 1.  

ሠለሞን አድማሱ

ማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ፈተና ማዕከል አስተባባሪ

 1.  

ገብረሚካኤል ገብረማሪያም

ቴክኖሎጂ ኢኒስቲቲውት ፈተና ማዕከል አስተባባሪ

 1.  

መሰረት አባይ

ህክምና ጤናሳይንስ ኮሌጅ ፈተና ማዕከል አስተባባሪ

 1.  

አሸናፊ ታፈሰ

ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ፈተና ማዕከል አስተባባሪ

 1.  

ይበልጣል አረጋ

ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ፈተና ማዕከል አስተባባሪ

 1.  

ወርቅነህ አለምነዉ

የህግ ት/ት ቤት ፈተና ማዕከል አስተባባሪ

 የፈተና ማዕከል ዝርዝር ተግባራት

 • ፈተናዎችን፤ወርክሽቶችን፤አሳይመንቶችን፤ኮርስ ሲለበሶችን ፤ሞጁሎችን ማባዛት
 • ለግቢው አገልግሎ ትየሚውሉ በርከት ብለው ሊባዙ የሚችሉ የተለያዩ ቅፆችን ማባዛት
 • የተከታታይ እና የአጠቃላይ ምዘና ውጤትን በተደራጀ ሁኔታ መያዝ
 • በፋኩልቲው/ኮሌጁ ውስጥ የሚገኙ እና ከሌላ ፋኩልቲ /ኮሌጅ የሚመጡ መምህራን በየሴሚስተሩ የያዟቸውን ኮርሶች መዝግ ቦመያዝ
 • የማጠቃለያ ፈተና የማባዣ ፕሮግራም ማውጣት፤ለሚመለከተው ማሳዎቅ እና በፕሮግራሙ መሰረት የማባዛት ስራ መስራት
 • የፈተና ማዕከሉ ሰራተኞች አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ ስልጠና እንዲያገኙ ማመቻቸት
 • ጥራት ያለው አገልግሎት ለተጠቃሚዎች መስጠት
 • በማዕከሉ የሚሰጡ አገልግሎቶች ፕሮፌሽናል፤ውጤታማ እናፈጣን እንዲሆኑ ማድረግ
 • ደንበኞች ስለማዕከሉ ያላቸውን አስተያየት በቃል፤ በአስተያየት መስጫ መዝገብ እናሳጥን እንዲሰጡ ማድረግ፡፡አስተያየቶችን በማጠናከር አሰራርን ማሻሻል
 • ፈተናዎች ሲባዙ በጥንቃቄ እና ሚስጥራቸውን በጠበቀ ሁኔታ ማከናዎን
 • የሚሰጡ አገልግሎቶች ከፋኩልቲው /ኮሌጁ ውሳኔ እና አቋም ጋር የተስማሙ መሆናቸውን ማ
  ረጋገጥ
 • ማዕከሉ የሚሰራቸው ስራዎች የሚሻሻሉበትን መንገዶች እና ዘዴዎች መዳሰስና መተግበር
 • ትምህርታዊ ፖሊሲዎች..ህጐችና አዋጆችን ለተማሪዎች እና ለአካዳሚክ ማህበረሰብ በቡክሌት እና በተለያዩ መንግዶች በማዘጋጀት እንዲደርሳቸው ማድረግ
 • በአካዳሚክካለንደሩ መሠረት ሥራዎችን ማከናወን
 • የማጠቃለያ ፈተናዎች በት/ክፍሉ ፈተና ኮሜቴ ታይተው እና ተገምግመው መምጣታቸውን ማረጋገጥ
 • የፈተና ባንክ በማዘጋጀት የማጠቃለያ ፈተናዎችን በሚስጢር በSoft Copy ማሰቀመጥ
 • አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከት/ክፍል ሀላፊዎች እና ከፋካልቲው ዲኖች ጋር ከፈተና ጋርየተያያዙ ሥራዎችን አብሮ መሥራት
 • ከማዕከሉ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የዩኒቨርስቲው ህጐች እና አዋጆችን መተርጐም እና መተግበር
 • የማእከሉን ሪፖርት አጠናክሮ በየሩብ አመቱ ለፋኩልቲው እና ለሚመለከተው መላክ
 • በፋካልቲው ዲኖች የሚሰጠውን ሌሎች ሥራዎችን ማከናወን