የእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ ጽሁፍ ትምህርት ክፍል ለአዲስ የፒ ኤች ዲ ተመራቂ ስታፍ አባላት የእንኳን ደስ ያላችሁ ፕሮግራም አዘጋጀ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ ጽሁፍ ትምህርት ክፍል ለአዲስ የፒ ኤች ዲ ተመራቂ ስታፍ አባላት የእንኳን ደስ ያላችሁ ፕሮግራም ሰኔ 03/2013ዓ.ም በማራኪ ግቢ አዘጋጀ።

በፕሮግራሙ የዲፓርትመንቱን ኃላፊ አቶ እንደሰው እሸቴን ጨምሮ በርካታ የትምህርት ክፍሉ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡ትምህርት ክፍሉን የተቀላቀሉ አዳዲስ አባላትም በፕሮግራሙ ትውውቅ ተደርጓል። የፒ ኤች ዲ የስታፉ አባላት ከፍ ማለት ለትምህርት ክፍሉ ብሎም ለዩኒቨርሲቲው የምርምር ተግባራት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡ እንዲህ አይነት ፕሮግራሞች መዘጋጀታቸውም የተመራቂዎችን ደስታ ከመጋራት ባሻገር የስታፉን ግንኙነት ያጠናክራል ሲሉም የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ ተናግረዋል፡፡
የእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ ጽሁፍ ትምህርት ክፍል አራት የስታፍ አባላትን በፒ ኤች ዲ በቅርቡ ማስመረቁ ይታወሳል፡፡
