የአለም የውሃ ቀን በቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ተከበረ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት በሀይድሮሊክና ውሃ ሀብት ምህንድስና ትምህርት ክፍል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ29ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ለ28ኛ ጊዜ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲአችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከበረውን የአለም የውሃ ቀን “ለውሃ ዋጋ እንስጥ” በሚል መሪ ቃል መጋቢት 22/2013 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ውሏል፡፡


የአለም የውሃ ቀንን የተለያዩ ሀገራት በተለያየ ሁኔታ ቢያከብሩትም በዩኒቨርሲቲያችን የተከበረበት ዋናው አላማ በዋናነት ውሃ የአለም ችግር ስለሆነ በተለይ የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግርን ለመፍታት ህዝቡ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሆነ የቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ም/ዲንና የአካዳሚክ ዳይሬክተር አቶ ዮሃንስ ሀ/ማሪያም በመክፈቻ ንግግራቸው ተናግረዋል፡፡
በትምህርት ክፍሉ ሃላፊ በአቶ እንዳልካቸው ጎሼ የውሃ ቀን አከባበርን በተመለከተ ፕረዘንቴሽን ከቀረበ በኋላ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡ በመሩሀ ግብሩ አዝናኝና ትምህርት አዘል ግጥምና ድራማ ቀርቧል፡፡ ዛሬ ማለትም መጋቢት 23/2013 ዓ.ም ተያያዥ የምርምር ስራዎች እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡