የቱሪዝም ምርት ማስፋፋት፣ ማቅረብና አዳዲስ የቱሪዝም ምርት አመራረትን የተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
የጎንደርዩ ኒቨርሲቲ የቱሪዝም ማኔጅመንት የትምህርት ክፍል ሀገር በቀል እውቀቶችን በመጠቀም አዳዲስ የቱሪዝም መስኮችን የማጎልበትና የመፍጠር ንድፈሃሳብን በተመለከተ፣ ሀገር በቀል የስዕል አሳሳል ጥበብን፣የብራና አዘገጃጀትና አጠቃቀምን እንዲሁም የሸክላ ሥራ ሙያዎችን በተመለከተ ከግንቦት 03-07/2013ዓ/ም ስልጠና መስጠቱ ይታወቃል።
በተያያዘም ለሰሜን ጎንደር ዞንና ለደባርቅ ከተማ አስተዳደር ለባህልና ቱሪዝም ባለሙያዎች የቱሪዝም ምርት ማስፋፋት፣ ማቅረብና አዳዲስ የቱሪዝም ምርት አመራረትን የተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ግንቦት 19 እና 20 በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የሰልጠና ክፍል ሰጥቷል፡፡

ይህ የማህበረሰብ አገልግሎት “New tourism product development and diversification” በሚል ርእስ የተዘጋጀ የንድፈሀሳብ ስልጠና ሲሆን፣የፕሮጀክቱ አስተባባሪ በሆኑት በመ/ር እንግዱ ገ/ወልድና በሌሎች አባል መምህራን ተሰጥቷል፡፡
