የማክሰኝት የወባ ምርምር ማዕከል ተመረቀ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና በተለያዩ አጋር አካላት ትብብር የተገነባው የጎንደር ዙሪያ ወረዳ የማክሰኝት የወባ ምርምር ማዕከል ህዳር 18/2010 ዓም በይፋ ተመርቋል፡፡
በምርቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻን ጨምሮ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፤የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ምክትል ፕሬዚዳንቶች፤ከጤና ጥበቃሚኒስቴርና ከክልል፤ከዞንና ከጎንደር ዙሪያ ወረዳ ጤና ቢሮ እንዲሁም ከማክሰኝት ከተማ ነዋሪዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፤ከአጋር አካላት ደግሞ Dr Harald Noedl Prof. at Medical Univresity of Viena, Australia, Mrs, Sophie Biguenet Medical Director, MMV and Mrs, Hilary Johnston from University of cape town እና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡
[widgetkit id=7662]
ዶክተር አበበ ገነቱ በሜዲካል ፓራሳይቶሎጂ ረዳት ፐሮፌሰርና የትምህርት ክፍል ኃላፊና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በኋላ የምረቃ ስነስርዓቱን በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት ባደረጉት ንግግር በ1946 ዓ.ም በጣና ዙሪያ በተከሰተው ከፍተኛ ጎርፍ ወባ ተከሰቶ በሽህ ሚቆተሩ ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑ አውስተው፤ችግሩን ለመቅረፍ የመካከለኛ ደረጃ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ በለሙያዎችን ለማሰልጠን በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ተቋም መከፈቱን ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም ከዛን ጊዜ ጀምሮ የህክምና አገልግሎት በመስጠትና የተለያዩ ምርምሮችን በመስራትና ዓለም አቀፍ ሀኪሞችን በማሰልጠን ላይ የሚገኘው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ ደረጃ በገዳይነቱ የሚታወቀውን የወባ በሽታን ለመቆጣጠር ከሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር አብሮ ለመሳራት ከ1ዓመት በፊት ስምምነት ላይ መደረሱን፤ በስምምነቱ መሰረትም ይህ የማክሰኝት የወባ ምርምር ማዕከል ግንባታው ተጠናቆና የውስጥ ቁሳቁሱ ተሟልቶ ለአግልግሎት መዘጋጀቱን ገልፀው፤ፕሮጀክቱ ለዚህ ይደርስ ዘንድ ድጋፍ ያደረጉትን አጋር አካላትና የዩኒቨርሲቲያችን የተለያዩ ክፍሎችና ባለሙያዎች አመስግነዋል፡፡
በመቀጠልም Dr Harald Noedl Prof. at Medical Univresity of Viena, Australia, Mrs, Sophie Biguenet Medical Director, MMV and Mrs, Hilary Johnston from University of cape town ቁልፍ ንግግር አድርገዋል፡፡ ከዚህ በመቀጠልም ድጋፍ ላደረጉ አጋር አካላትና ዬኒቨርሲቲያችን የተለያዩ ክፍሎችና ባለሙያዎች ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡
በመጨረሻም ዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻና Mrs, Sophie Biguenet Medical Director, MMV ሪቫን በመቁረጥ እና የማዕከሉ ውስጣዊ ይዘት ከተጎበኘ በኋላ የስነስርዓቱ ፍፃሜ ሆኗል፡፡ በተያያዘም 9ኛው የወባ ምርምር ኔት ወርክ ሲምፖዚየም ህዳር 19 እና 20 /2010 ዓም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል፤ ዝርዝር ዜናውን በሚቀጥለው ይዘን እንቀርባለን፡፡
ዘጋቢ በላይ መስፍን
የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት