አስደሳች ዜና
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ኮቪድ-19ን በመከላከል ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት የሚጀምሩበትን ቁመና የሚገመግም ቡድን ወደየተቋማቱ መላኩ ይታወቃል፡፡
የግምገማና ክትትል ቡድኑ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን መጥቶ ያለንን ዝግጁነት በተለያዩ መለኪያዎች መዝኖ ግብረ መልሱን ለመካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ አቅርቦ በስጋትና መልካም አጋጣሚዎች ጥልቅ ውይይትና ምክክር ተደርጓል፡፡
በመሆኑሞ የዓለም የጤና ድርጅትና የጤና ሚኒስቴርን መመሪያ በተገቢው መንገድ ተግባራዊ በማድረግ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማሩን እንደገና ለማስቀጠል የሚያስችል አቋም ላይ እንደሚገኝ በቡድኑ ግምገማ ውጤት ተረጋግጧል፡፡
ይህ ለመላው ተማሪዎቻችን፣ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ታላቅ የምስራች ነው የሚል እምነት አለን፡፡ ዩኒቨርሲቲያችንም በቅርቡ ተማሪዎችን ተቀብሎ መደበኛ ትምህርቱን የሚያስቀጥል ይሆናል፡፡
ሐገራችን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!