ንባብን ማህበረሰቡ ከባህሉ አንዱ ሊያደርግ እንደሚገባው ተገለፀ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብዕ ኮሌጅ የሶሲዮሎጂና ሶሻል ወርክ ትምህርት ክፍል ማራኪ ግቢ አልሙኒየም ህንፃ መሰብሰቢያ አዳራሽ መጋቢት 14/ 2010 ዓ/ም ወርሀዊ ሴሚናር አካሄደ፡፡ የማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብዕ ኮሌጅ ም/ዲን አቶ አይሸሽም ተረፈ፣ የትምህርት ክፍል ሀላፊዎች፣ የኮሌጁ መምህራን፣ የቋንቋና ስነ- ፅሁፍ ተማሪዎች ፣ የሶሲዮሎጂና ሶሻል ወርክ ተማሪዎችና የሌሎች ትምህርት ክፍሎች ተማሪዎች እንዲሁም በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት ጋዜጠኛና ደራሲ ዘነበ ወላ# The culture of reading in personal and societal development$ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ፅሁፍ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
[widgetkit id=8683]
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብዕ ኮሌጅ ከአለፉት ሁለት አመታት ጀምሮ ወርሃዊ ሴሚናር እያካሄደ ይገኛል፤ ለዚህም ተግባር ታዋቂ ምሁራንን በመጋበዝ፣ በተለያዩ ርዕሶች ላይ የተሰሩ ጥናታዊ ፅሁፎች እንዲያቀርቡ በማድረግ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተደራሽ ማድረግ ችሏል፡፡ በመሆኑም የመምህራንን፣ የተማሪዎችና የሰራተኞችን የንባብ ባህል ለማዳበር ወርሃዊ ሴሚናሮችን በማካሄድ፣ ወርሃዊ የንባብ ቀን ፕሮግራም በማውጣትና መምህራንን በማሳተፍ፣ የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ሁለንተናዊ አቅም ለማጎልበት/ በጥናታዊ ጽሁፍ አቀራረብ፣ በመጽሀፍ ግምገማ እና ትንተና አሰጣጥ/ ዙሪያ ለሚገኝ ዕውቀት ሽግግር እና ግንዛቤን ለማዳበር ኮሌጁ እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ የኮሌጁ ም/ዲን አቶ አይሸሽም ተረፈ ገልጸዋል፡፡ አቶ አይሸሽም አያይዘውም #አንድ ሰው የተማረ ነው ሊባል የሚችለው የንባብ ባህል አንዱ የህይወቱ አካል በማድረግ፣ ከተመረቀበት ሙያ ወጣ ብሎ ተዛማጅ እውቀትን በመገብየት ለሀገር፣ ለማህበረሰብ የሚጠቅም ስራ መስራት የሚችል ዜጋ መሆን ሲችል ነው፡፡$ ብለዋል፡፡
ጋዜጠኛና ደራሲ ዘነበ ወላ #ንባብ ማስተዋልን፣ አርቆ ማሰብን፣ ለሀገር ስልጣኔና እድገት ላይ የበኩልን ድርሻ መወጣትን ያስችላል፤ዝገትንም ይከላከላል$ ብለዋል፡፡ አያይዘውም የማህበረሰቡን የንባብ ባህል ለማሳደግ ከመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች መጀመር እንዳለበት፣ መምህራንም የማንበብ ልምድ የአላቸው መሆን እንዳለባቸው እና ሙያተኞችም ዝገትን ለመከላከል ከተመረቁበት ሙያ በተጨማሪ የታሪክና የስነ-ፅሁፍ እውቀት ቢኖራቸው ይመረጣል በማለት ገልፀዋል፡፡እንዲሁም ንባብን ማህበረሰቡ ከባህሉ አንዱ ሊደርግ እንደሚገባ በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡
ሪፖርተር፡- የሽመቤት ኃይሉ
ከህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት