ታላቅ የቁንጅና ዉድድር
የአፄ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዩጵያ ዝክረ-ሰማዓት 150ኛ ዓመት በዓል ከሚያዚያ 2-6/2010 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ በጎንደር ዩኒቨርስቲ የሚከበር ሲሆን የዝገጅቱ ድምቀት የሆነውም የሴት ተማሪዎች የቁንጅና ዉድድር መጋቢት 16/2010 ይካሄዳል፡፡
የዚህ ውድድር አሸናፊ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መጋቢት 23/2010 ዓ.ም በሚካሄደው የአማራ ክልል የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ደማቅ የአሸናፊዎች አሸናፊ የቁንጅና ውድድር ተሳታፊ በመሆን የወ/ሪት ተዋበች 2010 ማእረግን ትቀዳጃለች፡፡
ለተሳታፊችና አሸናፊዎች ዳጎስ ያለ ሽልማት ይበረከትላቸዋል፡፡
ማስታወሻ
የምዝገባ ቀን፡ መጋቢት 5-11/2010
የስልጠና ቀን፡ መጋቢት 12-14/2010
የውድድር ቀን፡መጋቢት 16/ 2010
የምዝገባ ቦታ፡ቱሪዝም ማኔጅመንት ት/ክፍል