በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በማራኪ ግቢ በምርምር ፕሮጀክት አዘገጃጀት የስነ-ምግባር ስልጠና ተሰጥቷል
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምር ህትመት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ምሳዬ ሙላቴ እንደገለፁት የስልጠናው ዋና ዓለማ የመምህራንን የምርምር ንድፈ ሃሳብ አቅምን ለማጎልበትና የምርምር ስነ-ምግባር ማለት ምን እንደሆነ ግንዛቤ መፍጠር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የምርምር ስነ-ምግባር ጥናቱ ሲታቀድ ጥናቱ ሲተገበርና ጥናቱ ሲጠናቀቅ ሊደረጉ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች በአግባቡ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ስነ-ምግባር ኦፊሰር አቶ ንጉሴ ይግዛው በበኩላቸው የምርምር ስነ-ምግባር የጥናቱን ተሳታፊዎች አጠቃላይ ግለሰባዊ መረጃዎችን ለመጠበቅ የሚያስችል ሲሆን የምርምሩን ሳይንሳዊ ዘዴና ቴክኒክ በአግባቡ ለመጠቀም ያስችላል ብለዋል ፡፡
ስልጠናው በማራኪ ግቢ ለሚገኙ ኮሌጆችና ትምህርት ክፍሎች ተሰጥቷል፡፡