በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ የመረጃ ትንተናና የምርምር ህትመት አዘገጃጀትን የተመለከተ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የድህረ ምረቃ ተመራቂ ተማሪዎች ጥራት ያለው የምርምር ውጤት እንዲያዘጋጁ የሚያስችል የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ከዛሬ ማለትም ግንቦት 16/2013 ዓ.ም ጀምሮ በመሰጠት ላይ ይገኛል። ስልጠናው በ2 ዙር የሚሰጥ ሲሆን ለ6 ቀናት እንደሚቆይም ታውቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲያችን የምርምር ዩኒቨርሲቲ ከመሆኑ አንፃር የድህረ ምረቃ ተማሪዎች የተለያዩ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም ችግር ፈች የሆነ ምርምር በመስራት የመመረቂያ ፅሁፋቸውን ማሳተም እንዲችሉ ለማገዝ ስልጠናው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ ኮሌጅ አካ/ዳይሬክተር ዶ/ር አስማማው አጥናፉ በመክፈቻ ንግግራቸው ተናግረዋል።

ሰልጣኞች ተመራቂ የማስተርስ ዲግሪ እና ስፔሻሊቲ ተማሪወች ሲሆኑ ከዚህ በፊት የፕሮፖዛል አዘገጃጀት ስልጠና እንደተሰጣቸው ያስታወሱት የኮሌጁ የድህረ ምረቃ አስተባባሪ ዶ/ር መኩሪያው አለማየሁ አሁን ደግሞ ጥራት ያለው የምርምር ህትመት ውጤት እንዲሰሩ የተማሪዎችን እውቀት ለማሻሻል በዩኒቨርሲቲአችን የተለያየ ልምድ ባላቸው ፕሮፌሰሮች ስልጠናው እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።
