በኢትዮጵያዊነት ፍልስፍና ዙሪያ ውይይት ተካሄደ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በየወሩ ታዋቂ ምሁራንን በመጋበዝ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሴሚናር ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍልም እውቁን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምሁር ፕ/ር ማሞ ሙጨን በመጋበዝ ታህሳስ 16/2010 ዓ/ም ማራኪ ግቢ በሚገኘው አዲሱ አዳራሽ የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ፣ መምህራን፣ ተማሪዎችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ሴሚናሩን አካሂዷል፡፡
[widgetkit id=7861]
ሴሚናሩን በንግግር የከፈቱት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ ሲሆኑ፣ “ፕ/ር ማሞ ሙጬ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክና ስለ ኢትዮጵያኒዝም ፍልስፍና ለማስተማር ፈቃደኛ ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲያችን በመምጣቸው በእኔና በኮሌጁ ስም አመሰግናለሁ” ብለዋል፡፡ ዶ/ር ካሳሁን አያይዘውም እለቱ በአዲሱ የኮሌጁ አዳራሽ ፕ/ር ማሞ የመጀመሪያ አቅራቢ መሆናቸውና ላለፉት ሶስት ዓመታት ስንመኘውና ስንለፋበት የቆየነውን በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር የነበረው አርካይብ ለጎንደር ከተማ ብቻ ሳይሆን ለአማራ ክልል፣ ለኢትዮጵያ፣ ለአፍሪካ ብሎም ለአለም የሚያገለግል፣ለተማሪዎቻችንና ለተመራማሪዎቻችን የመረጃ ምንጭ የሚሆን ትልቅ የታሪክ ምንጭ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን ለማምጣት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት፣ፕሮፊሰሮች፣ የትምህርት ክፍሉ መምህራንና የዞኑ አስተዳዳሪ በተገኙበት የተፈቀደበት እለት መሆኑ እለቱን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል ፡፡
ፕ/ር ማሞ ሙጬ # learning and knowing about Ethiopianism philosophy for making innovative Ethiopia $በሚል ርዕስ ጽሁፋቸውን አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ እና ስለ ኢትዮጵያኒዝም ሰፋ ያለ ገለፃ አቅርበው፣ ምሁራን የኢትዮጵያን ታሪክ መፃህፍትን በመፃፍ፣ ፊልም በመስራትና በመሳሰሉት ስራዎች ታሪካችንን በጥልቀት ማወቅና የማስተዋወቅ ስራ መስራት እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተው በማሳሰብ፣ ”ኢትዮጲያ ትልቅ ነበረች ትልቅነቷን ለመመለስ ኢትዮጵያኒዝምን እንወቅ፣ በኢትዮጵያዊነታችን እንኩራ፣ በአንድነትና በመደጋገፍ ምንም መስራት የሚያቅተን ነገር የለም” የሚል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ዘጋቢ፡- የሽመቤት ኃይሉ
አርታኢ፡- ይዳኙ ማንደፍሮ