በአዮዲን በበለፀገ ጨው አጠቃቀም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ማህበረሰብ አገልግሎት በህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ተቋም መምህራን በአዮዲን በበለፀገ ጨው አጠቃቀም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከጥቅምት 23-24/2013ዓ/ም ለላይ አርማጭሆ ወረዳ ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ ለጤና ባለሙያዎች፣ የሴቶች የጤና የልማት ቡድን መሪዎች፣ ለትምህርት ቤት የጤና ክበብ ተጠሪዎች፣ ከጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ጤናና ጤና ነክ ባለሙያዎች እና በአዮዲን የበለፀገ ጨው ነጋዴዎች በትክል ድንጋይ ከተማ አስተዳደር አዳራሽ በመሰጠት ላይ ነው፡፡
ስልጠናው በቤተሰብ ደረጃ በአዮዲን በለፀገ ጨው አጠቃቀም የሚያደናቅፉ የተሳሳቱ አመለካከቶችን፣ እምነቶችን እና የእውቀት ክፍተቶችን ለመሙላት ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና ሲሆን ፣ በአዮዲን ምንነትና በአዮዲን እጥረት የሚመጡ የጤና ችግሮች እንዲሁም የአዮዲን እጥረትን መከላከል እና ቁጥጥር ላይ በማተኮር ስልጠናው እየተሰጠ ነው፡፡**************************************
ሀገራችንን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ጥቅምት24/2013 ዓ.ም




