በአስተዳደር ዘርፍ መደቦች ላይ ዉይይት ተደረገ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀዉ የአስተዳደር ዘርፍ መደቦች የተፈላጊ ችሎታ ረቂቅ የዉሰጥ መመሪያ ላይ ሁሉም የዩኒቨርሲቲዉ ሰራተኞች በተገኙበት መጋቢት 14/2008 ዓ.ም በሳይንስ አምባ አዳራሽ ዉይይት ተካሄደ፡፡
ከቀኝ ወደ ግራ ሁለተኛዉ አቶ ሰለሞን አብርሐ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ም/ፕሬዚዳንት
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰሎሞን አብርሃ በዉይይቱ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት የዚህ ረቂቅ የዉሰጥ መመሪያ ዋና አላማ ስራንና ሰራተኛን በማገናኘት እና አሳታፊነትን በማረጋገጥ የመልካም የአስተዳደር ችግርን መቅረፍ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር አሁን በስራ ላይ ያለዉ በአንቀጽ 555/1999 የጸደቀዉ የአሰተዳደር ረቂቅ መመሪያ ጥቅል የሆኑ ነጥቦችን የያዘ በመሆኑ ሰራተኛዉ የተለያዩ ቅሬታዎችን እንዲያነሱ ሰለሚያደረግና ገልጽነት ሰለሚጎድለዉ አዲስ ረቂቅ መመሪያ ማዘጋጀት አሰፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ይህ ረቂቅ መመሪያ ለዉይይት መቅረቡን አቶ ሰለሞን አብርሀ ተናግረዋል፡፡ ረቂቅ መመሪያዉ የአንድን ባለሙያ ወይም ስራ ፈላጊ የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ መስፈርቶችን ያካተተ የዩኒቨርሲቲዉ የዉስጥ መመሪያ መሆኑን ጨምረዉ ተናግረዋል፡፡
ረቂቅ መመሪያዉ በተመረጡ ኮሚቴዎች አማካኝነት ከተዘገጀ በኋላ ህዳር 22/2008 ለእያንዳንዱ ዳይሬክቶሬትና የትምህርት ክፍል ተልኮ በአባላቱ እንዲገመገም የተደረገ ቢሆንም ግብረመልስ የሰጡት ክፍሎች ቁጥራቸዉ አነስተኛ መሆኑን ምክትል ፕሬዚዳንቱ ለተሰብሳቢዉ ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡
ረቂቅ መመሪያዉ በአቶ ወንደወሰን ዋኬኒ እና በአቶ ፈንታሁን ጫኔ ለተሰብሳቢዉ ከቀረበ በኋላ በረቂቁ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሰብሳቢ ሰራተኞች ተነስተዋል፡፡ ተወያዮች በረቂቅ መመሪያዉ መደሰታቸዉን ገልጸዉ የሚከተሉትን ጥያቄዎችን ጠይቀዋል፡፡ ከተጠየቁት ጥያቄዎች መካከል፡- ይህ የዉስጥ ረቂቅ መመሪያ በየጊዜዉ እየታየ የሚሻሻልበት ዉስን ጊዜ ተቀምጦለታል ወይ? በዉክልና የሰራንበት ለስራ ለምድ ይሆናልን? የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ኮሚቴዎች ለተጠየቁትና ምላሽ ለሚያስፈልጋቸዉ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዉ ማሻሻል የሚገባቸዉን ነጥቦች እንደሚያሻሽሉ ገለፀዋል፡፡ በመጨረሻም አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰሎሞን አብርሃ ይህ ረቂቅ መመሪያ ተፈጻሚነት የሚኖረዉ በአካዳሚክ ካዉንስል ተገምግሞ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒሰተር ሲያጸድቀዉ መሆኑን ተናግረዉ እስከዚያዉ ድረስ ግን በስራ ላይ ያለዉ መመሪያ እንደሚያገለገል አስረድተዎል፡፡
ዘጋቢ፡ ይላቅ አለባቸዉ
የጎንድር ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ከፍተኛ ሪፖርተር
አርታኢ፡ ደምሴ ደስታ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር