በስራ ዕድል ፈጠራ ለተሰማሩ ምሩቃን ሠልጣኞች ድጋፍ እየተደረገ ነው
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከሰሜን ጎንደር ዞን ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ መምሪያ እና ከአበዳሪ ተቋማት ጋር በመተባበር ከዞኑ ወረዳዎች ለተውጣጡ 200 ምሩቃን ሰልጣኞች የኢንተርፕርነርሽፕ ስልጠና በደልጊ ከተማ ሰጥቷል፡፡
አቶፈንታሁን ሥጦታው የሰ/ጎ/ዞ/ቴ/ሙ/ኢ/መምሪያ ኃላፊ
ሥልጠናው ከህዳር 23-27/2008 ዓ.ም ድረስ የተሰጠ ሲሆን ይህ ስልጠና ለስራ እድል ፈጠራ አጋዥ ኃይል መሆኑን የሰሜን ጎንደር ዞን ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ መምሪያ ኃላፊ አቶ ፈንታሁን ሥጦታው ገልፀዋል፡፡ የጣቁሳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መላኩ ዓለም በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት ስልጠናው ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው በሥራ ዕድል መሰማራት የጀመሩት የዞናችን የኢንተርፕርነር ሠልጣኞችን ውጤታማ ሊያደርግ የሚችል በመሆኑ ሰልጣኞች ስልጠናውን በብቃት ተከታትለው ወደ ተግባር መቀየር ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
የኢንተር ፕራይዝ ሰልጣኞች የጣቁሳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መላኩ ዓለም
አቶ ሠለሞን መስፍን የዩኒቨርሲቲው ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲያችን ከማስተማሩ ጎን ለጎን ግማሽ ሚሊዮን ብር በጀት መድቦ የኢንተርፕርነር ሺፕ ስልጠና በአዲስና በነባር የስራ ዕድል ፈጠራ ለተሰማሩ ምሩቃን ሰልጣኞች ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ ዓላማው የስራ ዕድል ፈጠራን ማበረታታት ሲሆን ቴክኖሎጂው ወደ ህብረተሰቡ ወርዶ የህብረተሰቡን ችግር መፍታት እንዲችል እና በየገጠሩ የታፈኑ የስራ ዕድል ፈጣሪዎች መውጣት እንዲችሉ ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፡ አቶ ሰለሞን አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው ከስልጠናው ጀምሮ እስከ ቴክለ,ኖሎጂ ሽግግር እና ውጤት ግምገማ ድረስ ድጋፍና ክትትሉን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡
አቶ ሰለሞን መስፍን የጎ/ዩ/ኢ/ት/ቴ/ሺ/ዳይሬክተር አቶ በአምላኩ ካሴ የጎ/ዩ/ቢ/ኢ/ኮ/ የዩ/ኢ/ት/ቴ/ሺ/አስተባባሪ
በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስርና የቴክኖሎጂ ሽግግር አስተባባሪ የሆኑት አቶ በአምላኩ ካሴ ቢዝነሱን አስመልክቶ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግም አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
//ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት//