በሥራ ቦት ላይ የሚደርሱ የሴቶች ጥቃትን ለመከላከል ሥልጠና ተሰጠ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ያዘጋጀው በሴት የመንግስትት ሰራተኞች በሥራ ቦታ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እንዴት መከላከል ይቻላል በሚል መሪ ሀሳብ ከታህሳስ 30/2012 እስከ ጥር 01/2012 የቆየ ስልጠና በዳባት ወረዳ ተሰጥቷል።

በስልጠናው በጎንድር ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ_ሰብእ ኮሌጅ የኢትዮጵያ ተሃድሶ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ተባባሪ ፕ/ር ቡሻ ታአ፣ የዳባት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ውበት ዘውዱ፣ በዚህ ስልጠና ላይ የጥናቱ ባለቤትና መምህር የሆኑት አቶ ናሆም እያሱ የተገኙ ሲሆን ከወረዳው የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ የመንግስት ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

በፕሮግራሙ ተባባሪ ፕሮፌሰር ቡሻ ታአ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኋላ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ውበት ዘውዱ ሥልጠናውን በይፋ አስጀምረውታል።

በመቀጠልም ሥልጠናው በሶስት አሰልጣኞች ከተሰጠ በኋላ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት አስመልክቶ የቡድን ውይይት በተሳታፊዎች ተካሄዷል፣ ማደማደሚያ ላይም ተደርሶ የውሎው ፕሮግራም ተጠናቋል።
የሕዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት