ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከምዕ/በለሳ ወረዳ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

DSC_0552ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በምዕ/በለሳ ወረዳ የምርምር ማዕከል በጥናት ያመረተውን 120 ኩንታል ምርጥ ዘር ለወረዳው በስጦታ መልክ ለማበርከት ከወረዳው ጋር የመግባቢያ ሰነድ ግንቦት7/2009 ዓ.ም ተፈራረመ ፡፡ በመግባቢያ ሰነድ መፈራረሚያ መድረኩ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ፕ/ር መርሻ ጫኔን ጨምሮ ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣መምህራንና ተመራማሪዎች እንዲሁም የምዕ/በለሳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበባው ዘለቀና ሌሎች ከወረዳው ግብርና ፅ/ቤትና ከማህበራት [...]

በተለያዩ የድንችና የሰሊጥ ዝርያዎች ላይ እየተሰሩ ያሉ የማህበረሰብ አገልግሎት የምርምር ማሳዎች ተጎበኙ

DSC_0480በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግብርናና ገጠር ትራንስፎርሜሽን ኮሌጅ መምህራንና ተመራማሪዎች የተዘጋጁ፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በምርምር የተገኙ የድንችና የሰሊጥ ዝርያዎችን የሚያሳዩ መስኖዎች በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና መምህራን ግንቦት 6&8/2009 ዓ.ም ተጎበኙ፡፡ በጉብኝቱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ፕ/ር መርሻ ጫኔ እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሆነ ማንደፍሮን ጨምሮ በርካታ መምህራንና ተመራማሪዎች ተገኝተዋል፡፡ የድንች መስኖ ማሳዎቹ የተዘጋጁት [...]

ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስን ሙተ ዓመት መታሰቢያ በተመለከተ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ (ሚያዚያ 12/8-15/2010 ዓ.ም

60f3bae11163የጥናት ወረቀት ጥሪ (call for papers) የመቅደላ መቶ ሀምሳኛ ዓመት በዓል ጎንደር ዩኒቨርስቲ የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስን ሙተ ዓመት መታሰቢያ በተመለከተ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ (ሚያዚያ 12/8-15/2010 ዓ.ም በቀጣይ 2010 ዓ.ም ሚያዚያ ወር ላይ 150ኛ ዓመት የአፄ ቴዎድሮስ ሙተ ዓመት በመቅደላ በስፋት ይከበራል፡፡ የመቅደላ ታሪካዊ ጦርነትና የንጉስ ቴዎድሮስ መሞት ለ19ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያና አፍሪካ አህጉር የወደፊት እጣፈንታን [...]

በቱሪዝም ዘርፍ ያጋጠሙ ችግሮችን፣ መልካም አጋጣሚዎችንና የተሻሉ ተሞክሮዎችን በጥናትና ምርምር መቃኘት ለመስኩ እድገት ጉልህ ሚና አለው ተባለ

DSC_0960የኢፌድሪ ባህልና ቱሪዝም ከአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ ከክልሉ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም በተለይ ደግሞ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ በመተባበር በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ አገር ዓቀፍ የባህልና ቱሪዝም ጥናትና ምርምር ጉባኤ አካሄደ፡፡ ጉባኤው “ባህልና ቱሪዝም ለሀገራዊ እድገት” በሚል መሪ ቃል ከሚያዚያ 18 – 20/2009ዓ.ም በጎንደር ከተማ ሳይንስ አምባ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ በጉባኤው የኢፌድሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር [...]