የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ፕሮግራም የመጀመሪያ ዙር ለሰልጣኞች የትውውቅ መርሃ ግብር ተካሄደ

በጎንደር ኒቨርሲቲ ካሉት አጋር ድርጅቶች ውስጥ መቀመጫውን ካናዳ ያደረገው የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ፕሮግራም አንዱ ነው፡፡ ድርጅቱ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ ለመስራት ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ እየዳበረ በመጣ የሀሳብ ስምምነት መሰረት በ2010 የትምህርት ዘመን ለአካል ጉዳተኞችና ማስተማር ለማይችሉ ድሃ ቤተሰብ ልጆች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የዕደሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ባወጣው የምልመላ መስፈርት መስከረም 27ና 28/2010 ዓ.ም በህክምና ጤናሳይንስ ኮሌጅ ተቀብሎ ያስተናገደ ሲሆን የዕለቱ ፕሮግራም የተጀመረው ተማሪዎችን በክብር በመቀበልና ምዝገባ እንዲያካሂዱ በማድረግ ነው፡፡ ዓላማውም ከሰሐራ በታች ባሉ ሀገሮች የስልጠና፣ የትምህርትና የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ድህነትን ለመቀነስ የታሰበ ነው ተብሏል፡፡

ለዚህ የመጀመሪያ ዙር ፕሮግራም የተመለመሉት 20 ወጣቶቸች በተለያዩ የአማራ ክልል ትምህርት ቤቶች ሲሆን የምልመላው ሂደትተማሪዎቹ የጻፉትን ማመልከቻ በማየት፣ በማመልከቻው የተካተተው ሃሰብ ትክክል ስለመሆኑ እስከሰፈራቸው ድረስ ሄዶ በማረጋገጥና ቃለመጠይቅ በማድረግ ነው፡፡

በ1999ዓ.ም የተመሰረተው የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ፕሮግራም በአፍሪካ አሀጉር ከሰሐራ በታች ያሉ ሀገራትን በመደገፍ ይታወቃል፡፡ በአፍሪካ ለአካል ጉዳተኛና በኢኮኖሚ ማነስ የመማር ዕድል ለማግኘት ችግር ውስጥ ለሚገኙ 450 ተማሪዎች በመጀመሪያና በሁለተኛ ድግሪ የዕድሉ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

በ2010 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ 20 ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተናገደው የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በእዓመቱ አስር ተማሪዎችን በመጨመር በመጨረሻው 7ኛ ዓመት ላይ ቁጥሩ 70 እንደሚደርስ የገለጹት በሶሾሎጅ እረዳት ፕሮፌስርና የስኮላር ሽፕ ፕሮግራሙ ማናጀር ዶ/ሚኪያስ አበራ ናቸው፡፡ ዶ/ር ሚኪያስ አክለው እንደገለጹት ወደፊት ለተማሪዎቹ እንደ ዊለቸር፣ሪከርደርና ማዳመጫዎች እንደሚሟሉና የሚጠቀሙባቸው ህንፃዎችም ምቹ እንደሚሆኑ አበራርተዋል፡፡

የተመለመሉት ወጣት ተማሪዎች ከአካል ጉዳትና ከድሃ ቤተሰብ የመጡ ቢሆኑም በቀጣዩ ዓመት ያላቸውን ብቃትና ተሰጥኦ ማሳየት እንዳለባቸው ይጠበቃል፡፡ይህ በሀገራችን የመጀመሪያው ሲሆን ተማሪዎቹ ምቹ አካባቢና የተሟላ የምግብ አገልግሎት አግኝተው የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደለባቸውም ይታመናል፡፡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲም እንዲህ ዓይነቱን ልዩና ለውጥ አምጭ ፕሮግራም እንዲካሄድ በማድረጉ ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ፈር ቀዳጅ በመሆን መሪነቱን ያሳየበት መሆኑ በውይይቱ ተገልጿል፡፡

ዘጋቢ፡-ሳሙኤል ማለደ

ትረጉም፡-በላይ መስፍን

ኤዲተር፡-ደምሴ ደስታ

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት